(ዓለምነው ሽፈራው፣ ጥቅምንት 09፣ 2006 ዓ.ም.)፦
ዛሬ የጥቅምት ፀሐይ በጠዋቱ ብልጭ አለች እና ከወጣች የምትመለስ አትመስልም ነበር። እኔ ከአንድ ባለእንጀራዬ ጋር ከቤት ወጣ ብለን ወደሱቅ ጉዞ ጀመርን። የምንፈልገውን ልንገዛ ከአንድ ሁለት ሦስት ሱቅ ተዘዋወርና ስንመለስ ጸሐያችንን እየሞቅን ምንም ተሽከርካሪ በማይኼድበት መንገድ ጉዞ ጀመርን። በዚያ ይጓዝ የነበረው ህዝብ መመልከት ልክ አመድ የተረጨ ጉንዳን ይመስላል። እኛም እየተጋፋን ጉዞአችንን ቀጠልን። ትንሽ እንደተጓዝንም አንዲት ጥበበኛ ነዳይ በጣም በጥበብ ትለምናለች።
ዛሬ የጥቅምት ፀሐይ በጠዋቱ ብልጭ አለች እና ከወጣች የምትመለስ አትመስልም ነበር። እኔ ከአንድ ባለእንጀራዬ ጋር ከቤት ወጣ ብለን ወደሱቅ ጉዞ ጀመርን። የምንፈልገውን ልንገዛ ከአንድ ሁለት ሦስት ሱቅ ተዘዋወርና ስንመለስ ጸሐያችንን እየሞቅን ምንም ተሽከርካሪ በማይኼድበት መንገድ ጉዞ ጀመርን። በዚያ ይጓዝ የነበረው ህዝብ መመልከት ልክ አመድ የተረጨ ጉንዳን ይመስላል። እኛም እየተጋፋን ጉዞአችንን ቀጠልን። ትንሽ እንደተጓዝንም አንዲት ጥበበኛ ነዳይ በጣም በጥበብ ትለምናለች።
ድምጽ አውጥታ ስለእግዚአብሔር እያለሽም አይደለም። ስለማርያም፣ ስለገብርኤል፣ ስለማንም እያለችም አልነበረም። እራሷን በአንዲት አፈር ሁሉ ተሸርሽሮ አልቆ ስሮቿ በሙሉ ፈጥጠው የሚታዪ እጽን መስላ እንጅ። ከሩቅ ሆነው ሲያዩት አንድ ቀለል ያለች ዛፍ ትመስላለች። ሲቀርቧት ደግሞ በበንድ ላላስተዋላት ለጌጥ የተሰራ ምስልን መስላም ታሳስታለች። እኔም ከባለእንጀራዬ ጋር እንዴ እንዚህ ነጮች ዛሬ ጀምረው የክሪስ ማስ ጌጣጌጥ መስራት መጀመራቸው ነው እያልኩኝ ወደ እሷ ቀረብን። ስንቀርብ ግን ብልጥ እና ብልህ የኔቢጤ ሆና አገኘኋት። በመንገዱ ከሚትመለመለው ሰው ግማሹ (በተለይ ወጣቱ ክፍል) ቆሞ እሷን ይመለከታል። በሞባይሉም በካሜራውም ፎቶ ያነሳል፣ ይቀርጻል። እኔም እነሱን ልምሰል አልኩና ቆምኩኝ፤ ፎቶም ማሳንቴን ተያያዝኩት።
እዚያ በቆምኩባቸው ጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሰው እሷን በማየት ፈታ ይልና ያለውን ጣል ያደርግላታል። እሷም እጆቿን በማንቀሳቀስ ትመርቃለች ወይም ታመሰግናለች።
እኔ ደግሞን ነዳያንን የማውቃቸው ስለእግዚአብሔር፣ ስለማርያም፣ ስለገብርኤል፣ ስለቅዱሳን ወ.ዘ.ተ. እያሉ በአንድ አካባቢ ብዙ ሆነው ሲለምኑ ነው። አንድም ቦታ ቢሆን እንዲህ ጥበብ በተሞላበት ሁኔታ ሲለምኑ አላየሁም። በኋላም ከባለእንጀራዬ ጋር ለምን ተባባልን። ሁላችንም ከይመስለኛል ውጭ መልስ አልነበረንም። ለመሆኑ ለምን ይሆን ሁሉም የኢትዮጵያ ነዳዮ በአንድ አይነት ስታይል የሚለምኑት? ጥበብ ጠፍቶባቸው? ወይንስ ማኅበረሰቡ ጥበብን ስለማያደንቅ እና ሰሚ ተመልካች የለንም ብለው ስለሚያስቡ? ወይንስ የሚለምኑት ስለቸገራቸው እና ሰዎች ሲለምኑ ስላዪ ብቻ? እንደ እኔ ግን እንዲያው ጥበብን ቀልቀል እያደረጉ ቢለምኑ ሰውንም ፈታ ያደርጉታል፣ እነሱም የተሻለ ሊገኙ ይችላሉ ብየ አስባለሁ። ችግሩ እኛ ኢትዮጵያዊን አንዱ አዲስ ነገር ሲጀምር ሌላችን ተከትለን ያንኑ መድገም እንወዳለን። አንዱ ሱቅ ሲከፍት ሱቅ መክፈት። አንዱ መኪና ሲገዛ ሌላውም ያንኑ አይነት መኪና መግዛት። አንዱ ምግብ ቤት ሲከፍት ሌላውም ምግብ ቤት መክፈት። እናም ነዳያኖቻችንም እንደዚህ አይነት ጥበብን አንዱ ቢጀም ሁሉም ተነስተው ይህንን የሚጀምሩት ይመስለኛል። ይህ ከሆነ ደግሞ ከነአሉን የከተማ መንገዶቻችን እንኳን ሙሉ በሙሉ በቆመ ምስል መሳይ ሰው ተሞልተው ማለፊ እንዳናጣም ስጋቴ ነው። ብቻ ጥበብ የተሞላበትን የልመና ዘዴ ብናስተምራቸው መልካም ይመስለኛል።
ሃይደልበርግ፣ ብሔረ ጀርመን
ሃይደልበርግ፣ ብሔረ ጀርመን
No comments:
Post a Comment