ከቶ ምን ልክፈልሽ ውዲታ እናቴ
ውለታሽ በዘብኝ ለምስጋና የሚሆን ቃል አጣ አንደበቴ::
ከሰው በላይ እንድሆን ያየሽው መከራ
ቢነገር አያልቅም ለአለም ቢወራ፡፡
እራስሽን ጥለሽ እኔን ተንከባክበሽ
ከሰው በታች ሆነሽ እኔን አኮፍሰሽ
ቢያመኝ ተሰቃይተሽ ብሎም ተጎሳቁለሽ
እዚህ አደረሽኝ ከሰው በታች ሆነሽ
ውዲታ እናቴ እግዜር ጤና ይስጥሽ
እኔ በምን አቅሜ በምን ላመስግንሽ፡፡
ውስጤ ተቃጠለ እንባንም አነባሁ
በጣሙን ከበደኝ ውለታሽን ሳየው
እግዜር ዕድሜ ይስጥሽ ከቶ ምን እላለሁ
ውዲቷ እናቴ አመሰግናለሁ፡፡
ምንጭ:- የወል
No comments:
Post a Comment