ሁሉም አንደየ አቅሙ ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ እያለ አለኝ የሚለውን ለብሶ፣ ከየ ቀየው ብቅ ብቅ ሲል ያለዉ ድባብ አጀብ ያስብላል። ግሩም የኢትዮጵያዊነት ባህል። ከዚያም ሁልጊዜ የኢትዮጵያ ታሪክ ሲነሳ፣ የማትለየዋ ቅድስት ወደሆነችው ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተ ከርስቲያን ጉዞው ይጀመራል። ጳጳሳቱ፣ ካህናቱ፣ ዲያቆናቱ ታቦቱን ይዘው ከቤተ መቅደሱ ብቅ ሲሉ፣ ይህ ህዝብም ከመዘምራኑ ጋር በመሆን "ታቦት በዉሥቴታ" እያለ ታቦቱን በማጀብ ጉዞዉን ወደ ባህረ ጥምቀቱ ይገሰግሳል። አቤት ይህን ጊዜ ያየው። ዓለም ቅልጥ ትል ይሆናል። በዓሉ መንፈሳዊ መሆኑ ተረስቶ እንድያው ጭፈራዉንም ያስነኩታል። አዛዉንቱ፣ ወጣቱ፣ ህጻናቱም ሳይቀር ታቦቱ የሚሄድበትን ቦታ ምንጣፍ በማንጠፍ፣ ቀጤማ በመጎዝጎዝ፣ ሽቶ በመረብረብ ሽር ርጉድ ሲሉ አለማየት ነው። ሊቃዉንቱ፣ የሰንበት ተማሪዎች የሚዘምሩት መዝሙርማ ነፍስን ዉስድ አድርጎ፣ በምድር ቀርቶ ከሰማይ መላእክት ጋር ያለ ነው የሚያስመስለው። እንዲህ እየተሆነ የየአድባራቱ እና ገዳማቱ ታቦታት በአንድነት ከባህረ ጥምቀቱ ይደረሳል። ታዲያ ይህ በዓል፣ ባህል እንኳን በህይዎት ላለ በመቃብርም እንኳን ትዝ ይላል።
በዚህ ጊዜ ወጣቶቹ ሌላም ነገር አላቸው። ሎሚ ዉርወራ። አንድ ጎረምሳ የምዎዳት ካለች ሎሚ፣ እንቦአይ ይወረውራል። ኮረዳዋም ብትሆን ይምትዎደው ካለ ከመወርወር አትቆጠብም። ብዙ ሰዎችም በንደዚህ አይነት ሁናቴ ተገናኝተው ኑሮአቸውን የሚገፉ አሉ።
ከዚህ በሁአላማ ሁሉ በዚያም በዚያም ወከባ ይሆናል። ሌሊቱን በሙሉ ካህናት ሊቃዉንቱ ስብሐቱን እንደ ዝናብ ስያፈሱት ያድሩና ወደ ቅዳሴ ይገባሉ። ሕዝቡም የቻለ ከታቦቱ አብሮ ሌሊቱን ያልጋዋል። ያልቻለ ደግሞ ከቤቱ አረፍ ብሎ ያድርና የአህያ ሆድ ሲመስል ጎዞዉን ወደ ታቦቱ ያደርጋል። ቅዳሰዉም ሲነጋ ያልቅና ወደ ጥምቀት ይሄዳል። ከዚህ በሁአል ያለዉን ትርምስ አታንሱት። ያም ያም ከበረከቱ ለማግኘት ግፊዉ በስመ አብ። ለነገሩ ግፊዉ የሚጀምረው ገና በጠዋቱ ቅዳሴው ሳይጠናቀቅ ነው። ቢሆንም ግን በረከቱ ብዙ ዉሃ በማግኘት ይመስል፣ ጥምቀቱ ሲጀመር ያለዉን ግፊ ተዉት።
በዓሉ የሚከበረው ለእኛ ሲል ወደዚህ ዓለም መጥቶ፣ በባህረ ዮርዳኖስ የዕዳ ደብዳበያችንን የቀደደበት የጌታችን የዚየሱስ ክርስቶስ ጥምቀት ነው። በዚህ በዓል ምስጢረ ስላሴ የተገለተበትም ነው። ዝርዝሩን በዚህ እለት ሊቃዉንቱ ሲያስተምሩት ምን ያክል አስድናቂ ነው። ዮሐንስ በባህረ ዮርዳኖስ ክርስቶስን ሲያጠምቅ፣ ከሰማይ በደመና አብ "የምዎደው ልጄ ይህ ነው" አለ። መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል መጥቶ በላዩ ላይ አረፈበት። በዚህ መልክ ነው አንድነት ሶስትነት የተገለጠው። ትልቅ የሆነዉን ትምህርት ከሊቃዉንቱ ቃል እንስማ።
እንዲህ እንዲህ እያለ ወደ በዓሉ እለት ከረፋዱ አምስት ስድስት ሰዓት ይደረሳል። ከዚያም ያ አምሮበት የወጣ ሕዝብ እንዲያ እንዳለ፣ ታቦቱን እንዳመጣ ዝማሬው፣ ምንጣፍ ማንጠፉ፣ ቀጤማ መጎዝጎዙ፣ ሽቶ መረብረቡ ሳይጎአደል ከቤተ መቅደሱ ያደርሰዋል። ከዚህ በሁአላ ነው ወደቤት መመለስ ያለው።
እኔም በአቅሜ ከዚህ ሁሉ እካፈል ነበር። ነገር ግን በዚህ ዓመት ለአይን እንኳን ማየት አልቻልኩም። ምን ይደረግ እንጀራ ሆነና። እንዲህ እያልኩኝ ከርሞ ሁለት ዓመት አድርሰኝ ብዬ በመሳል፣ ትዝታዬን ልቆአጭ።
ከበዓሉ በረከትም ይድረሰን!!! አሜን!!!
በዕለቱ ከሚዘመሩ መዝሙራትና ትምህርቶች በከፊል:
No comments:
Post a Comment