ለዓለም LEALEM
Home
Contact
About me
Wednesday, February 29, 2012
መዝሙር ዘአብይ ጾም
በጌቴሴማኒ (ማኅበረ ቅዱሳን )
በመዳን ቀን ጠራሁህ (ዘማሪ ይልማ ሀይሉ)
ኃይልህ ሲገለጽ በሰማይ
(ዘማሪ ይልማ ሀይሉ)
ዳግም ስትመጣ
አባታችን ሆይ
(አለሙ አጋ በገና)
ተው አለም ተመልስ
(ኪነ ጥበብ ወ/ቂርቆስ)
አንተ ይቅር በለን
(ኪነ ጥበብ ወ/ቂርቆስ)
እኔስ ለራሴ
(ኪነ ጥበብ ወ/ቂርቆስ)
ያችን የጥሪ ቀን አብረን እናስባት
(ኪነ ጥበብ ወ/ቂርቆስ)
(ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል Read More)
Wednesday, February 8, 2012
"እናትዬ"
ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህፀንሽ ይዘሽ፣
በዚህም ሳይበቃ በምጥ ተሰቃይተሽ፣
ሦስት ዓመት አጥብተሽ፣ ከጡትሽ መግብሽ፣
ደከመኝ ሳትይ በአንቀልባም አዝለሽ ፣
በፍቅር ያሳደግሽኝ ፍቅርሽን ለግሰሽ፣
እናትዬ ከቶ ምን ልክፈልሽ?
አንቺን እየራበሽ እኔን ያበላሽኝ፣
አንቺን እየጠማሽ እኔን ያረካሽኝ፣
አንቺ እየበረድሽ እኔን ያለበስሽኝ፣
አንቺን እያመመሽ እኔን ያፅናናሽኝ፣
ውዲቷ እናቴ አብዝተሽ ናፈቅሽኝ።
አንቺ ሳትማሪ እኔን ያስተማርሽኝ፣
ከተፈጥሮሽ ጥበብ እውቀት ያካፈልሽኝ፣
መክርሽ ገስጸሽ ለዚህ ያደረስሽኝ፣
ለወግ ለማዕረግ ለክብር ያብቃሽኝ፣
ወላጂቷ እናቴ ዘላለም ኑሪልኝ።
(ወደሚቀጥለው ገጽ ይዞራል Read More)
Newer Posts
Older Posts
Home
Subscribe to:
Posts (Atom)